ሁለት ወጣት ሴቶች


12202457_481419272026658_1716479871_n
ሁለት ወጣት ሴቶች ግማሽ አካላታቸውን ብቻ የሚሸፍን ልብስ ለብሰው ስብሰባ ቦታ ደረሱ።

ይህ የስብሰባው መሪ የተናገረው መልዕክት ነው። በጥሩ ፈገግታ ተመለከታቸውና እንዲቀመጡ ጋበዛቸው። ከዚያም እነዚህ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ሊረሱት የማይችሉት መልዕክት ተናገራቸው። ትኩር ብሎ አይናቸውን እያየ እንዲህ አላቸው፣
“ሴቶች ፈጣሪ የፈጠራቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ በሚገባ የተሸፈኑ እና እንዲሁም ለማየት እና ለማግኘት ብዙ ጥረት የሚጠይቁ ናቸው።

፩ አልማዞችን የት ነው የምታገኙአቸው? ከመሬት በታች ከብዙ ጥልቀት በሗላ ተሸፍነውና ተጠብቀው።
፪ ወርቆችን የት ነው የምታገአቸው ? ከማዕድናቶች በታች በትላልቅ ድንጋዮች ተሸፍነው ነው። እነሱን ለማግኘት ወደታች ብዙ ርቀት ጠንክራችሁ መቆፈር፣ መስራት እና መፈለግ አለባችሁ።

ከዚያም ፊታቸውን ትኩር ብሎ እያየ ንግግሩን ቀጠለ። “የእናንተ ሰውነት አስፈሪና ልዩ ነው። የእናንተ ሰውነት ከአልማዝ፣ ከወርቅ እና ከሌሎች የበለጠ ውድ እና ማራኪ ነው። ስለዚህ እናንተም በሚገባ ልትሸፈኑ ይገባል።
ንግግሩን ቀጠለ፣ ይህንን ውድ ሃብታችሁን ልክ እንደ አልማዝ፣ እና ወርቅ በሚገባ ከሸፈናችሁና በቀላሉ እንዳይገኝ ካደረጋችሁ ታማኞች እና አስፈላጊውን የማዕድን ማውጫ መሳሪያዎች ያላቸው ማዕድን አውጪ ድርጅቶች እናንተን ለማግኘትና ለዘመናት
የማዕድን ማውጣት ስራቸውን ለመስራት ወደ እናንተ ይጎርፋሉ።

በመጀመሪያ ከሃገራችሁ መንግስት( ቤተሰባችሁ) ጋር
ይገናኛሉ፣ ፕሮፌሽናል እና ህጋዊ ፊርማ (ህጋዊ ጋብቻ)ይፈራረማሉ። ነገር ግን የህንን ውድ እና ማራኪ ሃብታችሁን በሚገባ ባትሸፍኑት እና ባትጠብቁት ሁልጊዜ ህገወጥ ማዕድን አውጪዎች ወደ እናንተ እንዲመጡ እና ውድ ማዕድናችሁን በህገወጥ መንገድ እንዲያወጡት ትማርካላችሁ።

ከዚያም ምንም ሳይጥሩ እና ሳይደክሙ በቀላሉ ውድ ሃብታችሁን ይወስዳሉ ማለት ነው። ስለዚህ ሴቶች እባካችሁ ሰውነታችሁን በሚገባ ሸፍኑ። ይህን ካደረጋችሁ ፕሮፌሽናሎች እና ህጋዊ ማዕድን አውጪዎች እናንተን ያሳድዳሉ።”

ስለዚህ እስቲ ሁላችንም ሚስቶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን እና
ልጆቻችንን ሰውነታቸን በሚገባ ልብስ በሚገባ እንዲሸፍኑ እና እንዲከበሩ እናስተምራቸው።

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል
«ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ።»

Advertisements