ስለ ዲኦድራንትዎ ምን ያህል ያውቃሉ?


10846402_738938606196881_8000614292932115270_nመቼም ብዙዎቻችን ጠዋት ከቤታችን ከመውጣታችን በፊት ከታጠብን እና ከለበስን በኋላ ዲኦድራንት መጠቀም የተለመደ ነው።
ስለ ዲኦድራንትዎ ምን ያህል ያውቃሉ? እስቲ ስለ ዲኦድራንት ለያውቁ የሚገባዎትን አስር ነገሮች እነሆ እንበላችሁ።
1 ዲኦድራንት ባክቴሪያ ይገላል
የሰው ልጅ ላብ ሽታ አልባ እንደሆነ ያውቃሉ? የሰውነት ሽታን የሚያመጡት ባክቴሪያዎች ናቸው ዶኦድራንት ደግሞ እነኚህን ባክቴሪያዎች ሊገል የሚችል እና በምትኩ ጥሩ ሽታን እንዲሰጥ የሚያስችል ንጥረ ነገር ይዟል።
2 ዲኦድራንት ላብን ማቆም አይችልም
ዲኦድራንት የሰውነታችንን የላብ መጠን በ 20 በመቶ ብቻ ነው ማቆም የሚችለው።
ሆኖም አንዳንድ ልዩ ዶኦድራንቶች እስከ 30 በመቶ የማቆም አቅም አላቸው።
3 የተለያዩ ዲኦድራንቶችን በተወሰኑ ወራቶች መሞከር
አንድ አይንት ዲኦድራንትን ደጋግሞ መጠቀም ሰውነታችን ከዲኦድራንቱ ጋር እንዲላመድ ስለሚያደርገው ውጤቱን ያነሰ ያደርገዋል።
ቢያንስ በስድስት ወር አዳዲስ ዲኦድራንቶችን መጠቀም ጥሩ ጠረን እንዲሁም ውጤት እንድናገኝ ይረዳናል።
4. ዲኦድራንቶት ፆታን አይለይም
በሴት እና በወንድ ዴኦድራንቶች መካከል ያለው ብቸኛ ልዩነት የሽታ እና የአስተሻሸግ ነው።
ከዛ በተረፈ ውሰጡ የሚይዘው ንጥረ ነገር አንድ አይነት ነው።
ስለዚህም ቸኩለው የሴት ወይም የወንድ ዴኦድራንት ቢጠቀሙ ጥቅሙ አንድ አይነት ነው።
5 ዲኦድራንት ልብስ ለይ የሚተወውን ቢጫ ቅሪት ማስቀረት ይቻላል
ብዙዎቹ ዲኦድራንቶች የአሉሙኒየም ማሸጊያ ውስጥ ተደርገው መምጣታቸው የአሉሙኒየሙ ንጥረ ነገር ከላብ ከቲ ሸርት እና ከቆዳ ጋር ሲገናኝ ቢጫ ቅሪትነ ይፈጥራል።
ይህንንም ለመከላከል በአልሙኒየም ያልታሸጉ ዶኦድራንቶችን መጠቀም ይመከራል።
6 ወደ መጥታ ከመሄድ በፊት ዲኦድራንት መቀባት
.ማታ ዲኦድራንትን መቀባት ዋና ጥቅሙ በላብ ምክንያት ሰውነታችን ስለማይዘጋ የዲኢድራንቱ ጥቅም ሰውነታችን ሙሉ በሙሉ እንዲያገኝ እናረገዋለን ጥሩ ጠረኑም ለእንቅልፍ ይረዳል።
7 ሁሉም ሰው ዶኦድራንት ላያስፈልገው ይችላል
የሁሉም ሰው የሰውነት ፀባይ ስለሚለያይ እንደ ሰውነታችን ፀባይ ዲኦድራንት ማዘውተር ወይም ደግሞ አለመጠቀም እንቸላለን።
8 ዶኦድራንትን ሌሎች ተፈጥሮአዊ በሆኑ ነገሮች መተካት ይቻላል
ሌሎች ተመሳሳይ ንጥረ ነገሮችን እና ተፈጥሮአዊ አትክልቶችን በመጠቀም ዲኦድራንትን መተካት ይቻላል።
9 ዲኦድራንት የእግር ድርቅት ላለባቸው ይመከራል
የእግር ድርቀት ካለቦት የእግሮ የታችኛው ክፍል ላይ ማታ ሊተኙ ሲሉ አድርገውት መተኛት።
አላስፈላጊ የእግር ጠረንን ከመከላከሉ ባኛገር የእግር ድርቀትን ይከላከላል።
10 በጫማ ምክንያት የሚመጣን ህመም ይከላከላል
አዲስ ጫማ በሚደረግ ሰአት በተለይ በበሴቶች ላይ ጣትን የማመም ስሜት ይከሰታል።
በእግሮት ጎን እና ጎን ላይ በመጠኑ ዶኦድራንት መቀባት ጫማው ከሚፈጥረው ህመም ይከላከላል።
ምንጭ፦ዌልነስቢን

Advertisements