(ሰበር ዜና) ቴዲ አፍሮ ከሃገር እንዳይወጣ ታገደ


10359173_262838070567454_2140780313862814430_nበአውሮፓና የተለያዩ የሩቅ ምስራቅ አገራት የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ለማቅረብ ወደ ውጭ ሃገር ሊወጣ የነበረው ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከሐገር እንዳይወጣ መታገዱን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የታማኝ ምንጮች መረጃ አመለከተ። ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርቱን በፊንላንድ ሄልሲንኪ በነገው እለት ይጀምራል ተብሎ የነበረ ሲሆን የሙዚቃ ባንዶቹ አባላትና ማናጀሩ እዛው ፊላንድ ቢገቡም ቴዲ በደህንነቶች ከሃገር እንዳይወጣ በመታገዱ የተነሳ የነገው የፊንላንድ ኮንሰርት መሰረዙን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
ከጥቂት ወራት በፊትም ቴዲ አፍሮ ወደ አሜሪካ ሊመጣ ሲል እንዲሁ በደህነንቶች ተይዞ በኤርፖርት ሲጉላላ እንደቆየና በኋላም ወደ ውጭ እንዲወጣ እንደለቀቁት ያስታወሱት የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች፤ በአሁኑ ጭራሹኑ እንዳይወጣ ፓስፖርቱን ውስደውበታል ብለዋል። ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የቴዲ አፍሮ ፓስፖርት ያልተመለሰለት ሲሆን ወደፊት እንዲወጣ ይፍቀዱለት አይፈቀዱለት የታወቀ ነገር የለም ብለዋል።
የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ቴዲ ለምን ከሃገር እንዳይወጣ እንደታገደ የተገለጸለት ነገር የለም:።
በሄልሰንኪ ፊላንድ የቴዲን መምጣት በጉጉት የሚጠባበቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በርካታ ሲሆኑ አዘጋጆቹም ቴዲ ይመጣል በሚል በርካታ ትኬቶችን ሸጠው ነበር። ሆኖም ግን ኮንሰርቱ በመሰረዙ የተነሳ ትኬቱን የገዙ ሰዎች ገንዘባቸው እንደሚመለስላቸው አዘጋጆቹ በቪድዮ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። ቪድዮውን ይመልከቱት።
በዚህ ዙሪያ የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆነውን አቶ ዘካሪያስ ጌታቸውን ዘ-ሐበሻ ለማነጋገር እየሞከረች ሲሆን ማናጀሩን እንደገኘነው ሃሳቡን ለአንባቢዎቻችን እናካፍላለን። በተረፈ ወያኔ ብልጥ ነው  በመስቀል አደባባይ የታሰበውን ሰላማዊሰልፍ ለማደናቀፍና የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየርሲባል  ቴዲ አፍሮን ከአገር አዳይወጣ አገደ ።

Advertisements