ከ1 ሺህ 300 በላይ የሃይማኖት ድርጅቶችና ማህበራት በኢትዮጵያ


አዲሰ አበባ ህዳር 9/2007
IETIA_Religion_Subcategory_newበኢትዮጵያ ከ1 ሺህ 300 በላይ የሃይማኖት ድርጅቶችና ማህበራት ህጋዊ ምዝገባ አግኝተው በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ::

በአገሪቱ ለተጀመረው የሰላም እሴት ግንባታ ውጤታማነት የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶችና ማህበራት የሚጠበቅባቸውን ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።

በሰላም እሴት ግንባታ ማሰልጠኛ ዙሪያ በአገሪቱ ለሚገኙ የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶች እና ማህበራት ዛሬ በአዲስ አበባ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።IETIA_Religion_Subcategory_new

በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖቶችና እምነት ጄነራል ዳይሬክተር አቶ ሃጂ አሊ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንዳሉት የሃይማኖት ማህበራት እና ድርጅቶች የተጀመረውን የሰላም እሴት ግንባታ ውጤታማ ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል፡፡

“በሰላም አብሮ የመኖር ታሪካችንን በማጎልበት ለቀጣይ ትውልድ ማስረከብ የሚቻለው የሁሉም ሃይማኖት ማህበራት እና ድርጅቶች ለተከታዮቻቸው ስለ ሰላም እና መቻቻል መስበክ ሲችሉ ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

እንደ አቶ ሃጂ ገለጻ አገሪቱ የነበራትን መጥፎ ታሪክ በመፋቅ ላይ ስትሆን ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ለማሳካት የሚታትሩ አካላትን የየእምነቱ መሪዎችና ተከታዮች በጥብቅ መከታተል ይኖርባቸዋል።

በሰላም እሴት ግንባታ መጽሃፍ ስልጠና ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኢትዮጵያ ሴኬም ወንጌል አገልግሎት ሚኒስትሪ ስራ አስኪያጅ መጋቢ ሃዲስ ዳመሳ ደበሌ እንዳሉት የሰላም እሴት ግንባታ አጀንዳ የመንግስት ብቻ አይደለም።

የሰላም እሴት ግንባታ መጽሃፉ ከቤተክርስቲያናቸው አስተምህሮ ጋር ተመጋጋቢ በመሆኑ ለምዕመናኑ ስለ ሰላም ለማስተማር ትልቅ ግብአት እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።

የቅድስት ልደታ ማሪያም ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መስፍን ወርቁ በበኩላቸው ማህበራቸው ቅዱስ መጽሃፍም ስለ ሰላም እንድንሰብክ የሚያስገድደን በመሆኑ ለተከታዮቻችን ስለ መቻቻልና ምዕመናኑ የሌሎችን እምነትና አስተሳሰብ ማክበር እንደሚኖርባቸው እናስተምራለን ብለዋል።

ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብረው የኖሩ የአገሪቱ ህዝቦች በመካከላቸው ያለው መቻቻል ቀጣይነት እንዲኖረው የሃይማኖት ማህበራትና ድርጅቶች የማይተካ ሚና እንዳለባቸው ያስታወቁት አቶ መስፍን የሰላም እሴት ግንባታ ማሰልጠኛ መጽሃፉ ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር ምንም አይነት ቅራኔ እንደሌለው ገልጸዋል።�

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነትና ዶክመንቴሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ መስዑድ አደም የሰላም እሴት ግንባታ መጽሃፍ ከሁሉም እምነቶች የሃይማኖት አስተምህሮት ጋር በማይጣረስ መልኩና የሁሉም እምነት መሪዎች፣ ሊቃውንቶች እና የመንግስት አካላትን ባሳተፈ መንገድ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

የሰላም አሴት ግንባታ መጽሃፍ ዝግጅት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው በአገሪቱ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የአክራሪነትና የሽብርተኝነት ዝንባሌዎች በመታየታቸውና ይህንንም አደጋ በጋራ ለመመከት ተመሳሳይ አመለካከት ለመያዝ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

Source : ENA

– See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=2555#sthash.z26LfU7R.dpuf

Advertisements