መቼ ነው እውነት ምታወራው? መቼ ነው በሰው ስቃይ ማላገጡን ምታቆመው?


by አርአያ ተስፋማሪያም
አቤ ነፃ ወጣ!
1979671_10202743492978316_3310241985986880154_nበዋሽንግተን ዲሲ በዛሬው እለት በዋለው ችሎት ድምፃዊ አበበ ተካ በነፃ እንዲሰናበት ፍ/ቤቱ ወስኖዋል። ከፍርዱ በኋላ በአበበ ንግግር ብዙዎች በእንባ ተራጭተዋል።በርካታ አርቲስቶች፣ የአበበ ተካና ቤተሰቡ ወዳጅ ኢትዮጵያውያን ችሎቱን ሲከታተሉ የሰነበቱ ሲሆን በተላለፈው ውሳኔ ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር አበበ ከፍተኛ መስዋእትነት ለከፈለበት ፍቅርና ትዳር ፈጣሪ ሰላምና እርቅ አውርዶ ማየት እንደሚሹ ከልብ በመነጨ ስሜት ምኞታቸውን ገልፀዋል። በዲሲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለአበበ ጨዋነት፣ ለፍቅር፣ ለትዳሩና ለልጆቹ እጅግ ታማኝና ጨዋ ሰው እንደሆነ ሲናገሩ በአክብሮት ጭምር ነው። በዚህ አጋጣሚ ሰይፉ ፋንታሁን ደጋግሞ ያን ሁሉ የፈጠራ ክስ ድርሰት እየደረደረ ማላዘኑ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን ብዙዎች ገልፀዋል። በአበበ ተካ ላይ ሰይፉ ያለው ክስ ጨርሶ እንዳልተመሰረተ ብቻ ሳይሆን እንዳልታሰበ ሊታወቅ ይገባል። እንደ ሰይፉ ክስና ምኞት ቢሆንማ ኖሮ አበበ “ከአሜሪካ ተባሮዋል፣ እድሜ ልክ ተፈርዶበታል.”፤ ምን የሚሉት መጥፎ “ምኞት” ይሆን?..አገር ቤት ፍትህ አጥተው ስለሚሰቃዩት ወገኖች አንድ ነገር ሰይፉ ሊነግረን ይችላል!?.. ለማንኛውም የአበበና ባለቤቱን የወደፊት ሰላምና እርቅ (በመመኘት) ሲባል የተፈጠረውን ከመግለፅ እቆጠባለሁ። ቢሆንም የተፈጠረው ነገር በማንኛውም ትዳር ሊከሰት የሚችል ያለመግባባት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። «ድሬ ቲዩብ» የሰይፉን አንድ ወገን ሰምታችሁ ስታሰራጩ የነበረው አግባብ ያልሆነና ስህተት እንደነበረ መረዳት አለባችሁ። ድምፃዊው ነፃ እንደወጣ ሁሉ 3 ልጆች ያፈሩበትና ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት ትዳር ፈጣሪ እርቀ ሰላም እንዲያወርድበትና ወደቀደሞ ፍቅራቸው እንዲመልሳቸው መልካም ፈቃዱ ይሁን!!..Abebe Teka

Advertisements