ትሮክ
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)
stroke_hemorrhagicስትሮክ በመባል የሚታወቀው የህመም አይነት በመላው ዓለም እንዲሁም በሀገራችን እጅግ እየተበራከተ የሚገኝ እና ከፍተኛ
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የህመም አይነት ነው፡፡
ስትሮክ ሊከሰትባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው
✔ በጭንቅላት ውስ በሚከሰት የደደም መፍሰስ
✔ ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ
ስትሮክ ከተከሰተ በኋላ በአፈጣኝ ወደ ህክምና መውሰድ እና ህክምናውን ወዲያውኑ መውሰድ የታማሚውን ሊደርስበት የሚችለውን የጉዳት ክብደት መቀነስ እና የማገገም ሁኔታውን ሊፋጥን ይችላል፡፡
* ለበሽታው ሚያጋልጡ ሁኔታዎች
✔ እድሜ፡
በእድሜ በገፋን ቁጥር በስትሮክ የመጠቃት እድላችን ይጨምራል
✔ ጾታ፡
ስትሮክ በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያመለክታሉ
✔ በዘር ሊተላለፍ እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ
✔ የደም ግፊት መጨመር
✔ የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
✔ ሲጋራ ማጤስ
✔ በስኳር ህመም መያዝ
✔ የሰውነት ክብደት መጨመር
✔ ከዚህ ቀደም በስትሮክ መጠቃት
* የስትሮክ ህመም ምልክቶች
ስትሮክ በተከሰተ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የአንጎል ህዋሶች መሞት ይጀምራሉ ይህም የሚከተሉትን አይነት ምልክቶች ያስከትላል
✔ ለመራመድ መቸገር ወይም ሚዛን አለመጠበቅ
✔ ለመነጋገር መቸገር
✔ የሰውነት ክፍል (እጅ ወይንም እግር) ያለመታዘዝ
✔ የአይን ብዥታ
✔ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት
✔ ግራ የመጋባት ስሜት
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በአቅራቢያው በሚገኘው ሰው ከተመለከቱ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ተገቢ ነው።
* ስትሮክን የመከላከያ መንገዶች
የመጀመሪያ እና ቀዳሚው የመከላከያ መንገድ ስለበሽታው ምንነት እና ስለሚያስከትለው ጉዳት ማወቅ ነው፡፡
ስትሮክን የመከላከያ መንገዶች ከእለት ተእለት የአኗኗር ሁኔታችን ጋር የተያያዘ ነው፡፡
► የደም ግፊት መጠናችንን ማወቅ እና የደም ግፊታችን ከፍተኛ ከሆነም በሚገባ ለመቆጣጠር መሞከር፡፡ የደም ግፊት መድሃኒት የምንወስድም ከሆነ በትክክል እና ያለማቋረጥ መውሰድ፡፡
► የስኳር ህመም ተጠቂ ከሆኑ የስኳር መጠኖን መቆጣጠር
► ጭንቀትን ማስወገድ
► ሲጋራ አለማጤስ
► የአልኮል መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ መጠጦችን አለመውሰድ
► የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ
► ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያለማዘውተር
► በቀን ለ 30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም የእግር መንገድ መሄድ
► የሰውነት ክብደትን መቀነስ፡፡
ጤና ይስጥልኝ