የቴዲ አፍሮና የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ምናባዊ ቆይታ >>


1551535_10203892596488371_6466588169066516854_nክፍል ፩

……….ቴዲ አንድ ዘመናዊ መኪና እያሽከረከረ ወደ የሚያምር ግቢ ሲገባ አይቼው ተከተልኩት እሱም ዞር ብሎም አላየም
ወደ አዳራሹ ለመግባት አመነታሁ ስገባ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ቁጭ ብለዋል ቴዲን ሲያዩት ከተቀመጡበት ተነሱ መላ ፊታቸውም በደስታ ተዋበ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ቴዲ ለአይን የሚማርክ በወርቅ የተለበጠ መቀመጫ ለይ ተቀመጠ ።
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴም ለድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ያደረጉለትን አቀባባል ባየሁ ጊዜ ማመን ነበር ያቃተኝ << እውነትም ቴዲ ታላቅ ሰው ነው >> አልኩ :: ከተራው ሰው ጀምሮ እስከ ትላልቅ ሰዎች የሚሰጡት ክብር ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ብዬ አሰብኩ ።
የውይይታቸውን ምዕራፍ የከፈቱት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ነበሩ ። ጣታቸውን ወደ ቴዲ ቀስረው ” አንተ የሀገር ኩራት ለወገንህ ሀሳቢና ተቆርቋሪ የፍቅርና የአንድነት መግለጫ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነህ ። በእናት ማህፀን እያለህ ነው እግዚአብሔር የባረከ በተለይ የማታውቀውን ነገር ለማወቅ የምታሳየው ያላሰለሰ ጥረት ይደነቅልሃል ። ያንተ መፈጠር ለዚህች ምድር ለበጐ ነው ። ገና ብዙ ትሰራለህ የዚህች ሀገርም መልካም ስጦታዋ ነህ ከፈጣሪ በተሰጠ የጥበብ ሙያ በሚያምረውና ልብን በሚያቀልጠው ማራኪው ድምፅህ ለሀገርህና ለወገንህ የምታበረክታቸው ህያው ስራዎች ያንተን ማንነት ያስረዳሉ ። ”
ቴዲም በድንገት ከተቀመጠበት በመነሳት ” ጃንሆይ ሙዚቃ ለእኔ ህይወቴ ነች የልቤን እውነት የምሰብክባት በነፃነት ሀሳቤን የምገልፅባት የአምላኬ ልዩ ስጦታዬ ነች ። ከፈጣሪ በተሰጠኝም ሙያዬ ሀገሬንና ወገኔን አገለግላለሁ ።” በረጅሙ ተነፈሰ…………………… ከተነሳበት የሚማርክ ወንበር ላይ መልሶ ተቀመጠና ንግግሩን ቀጠለ ፣
<< እውነትን ከመናገር ወደኋላ አልልም ፣ ከሀሰት ጋር ህብረትን አላደርግም ። >>
ቴዲን ” ይዅውልህ ልጄ ” አሁት ጃንሆይ ” ለበርካታ ጊዜ ልብ ብለን ተመልክተንሃን ። ለያዝከውም የጥበብ ሙያ ልዩ ፍቅር ያለህ ነህ ቅንነትን የምትወድ ፣ በፍቅር የምታምን ፣ ሰላምን አብዝተህ የምትሻ ፣ ለኢትዮጵያ ከፈጣሪ የተሰጠህ በረከቷ ነህ ፤ አንተ በምታቀነቅናቸው የዘፈን ስራዎች ብዙ ነገሮች ይለወጣሉ ።
” ልብ በለኝ ልጄ……………….ዝናን በአግባቡ ለማይዝ ዝነኛ ሰው ዝና የመውደቂያው ጦስ ነች ። አንተ ገን ወገንህን አብዝተህ የምትወድ ፣ ለሀገርና ለባንዲራህ የምትቆረቆር ፣ ታላቅ ዝና አለኝ ብለህ ራስን በትዕቢት ያልወጠርክ ፣ ሀሳብህ ሁሉ ቅን የሆነ ፣ ለስኬታማነት ቀን ከሌሊት የምትጥር ፣ የአንበሶች አንበሳ ነህ ፤ ቅንነት መልካም ነው ብለህ ሁሉን ነገር ለበጐ የምትቀበል የፍቅር ሰው ከመሆንህም በላይ ለሠዎች መልካም ተምሳሌት ነህ ።”
ቴዲ የቀኝ እጁን ጉንጩ ላይ አስደግፎ የጃንሆይን ንግግር ልብ ብሎ ያዳምጣል በድንገት << እግዚአብሔር ታላቅ ነው ሀይልና ብርታቱም ከማንም በላይ ነው >> አለና ከተቀመጠበት ተነስቶ ፊት ለፊት የተቀመጠውን ባንዲራ አነሳ ።
” ጃንሆይ ገና ወደ ፊት የሚገርሙና የሚደንቁ ወርቃማ ስራዎችን እንደምሰራ አምናለሁ ፤ ከልጅነቴም ጀምሮ ትልቅ ትልቁን ነው የምመኘው ፤ የምመኘውንም ነገር ሁሉ እውን ለማድረግ እጥራለሁ ፤ ከሁሉም በላይ በእኔ ልብ የነገሰውን ፈጣሪዬ ብርታቴ ስለሆነ ህልሜን እውን ያደርግልኛል ። ” ቴዲ ያነሳውንም ባንዲራ ከፍ አድርጐ ” ይህ ባንዲራ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አለበት ” ብሎ በሀሳብ ሲቆዝም
ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ከተቀመጡበት በወርቅ ከተለበጠው ወንበር ላይ ሆነው የለበሱት ነጭ በነጭ ልብስ ግርማ ሞገስን አከናንባአቸዋል ። ብዙ ጊዜ ቴዲን ሲጠሩት << ልጄ >> ብለው ነውና ” ልጄ ” አሉት ፤ ቴዲም ” አቤት ” ለማለት ሰከንድ አልፈጀበትም ነበር ።
……………………………..ይቀጥላል
ምንጭ :- የቴዲ አፍሮ የታላቅነት ምስጢር