የቴዲ እና የኮካኮላ ኩባንያ ጉዳይ ሁለት ነገሮችን ያሳየናል


ጌታቸው በቀለ

1/ ቅድምያ ለዜጎቹ እና ለሀገሩ ጉዳይ የሚሰጥ መንግስት ቢኖር ኖሮ የቴዲ ጉዳይ እንዲህ እንደዋዛ የሚታለፍ አልነበረም። ነገሩ በሌላ ሀገር እንበል በሱማሌ ላይም ቢሆን ኖሮ 10359173_262838070567454_2140780313862814430_nየተፈፀመው ፕሬዝዳንቱ ሳይቀር መግለጫ እና ግልፅ ደብዳቤ ለኮካኮላ ኩባንያ ይፅፉ ነበር።ምን ይሄ ብቻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በግልፅ ”ጉዳዩ የሀገር ገፅታ ላይ ተፅኖ አለው ይህ ዓለም አቀፍ ዘረኝነት ነው” ብለው ይከራከሩ ነበር።ግን ይህ የሚሆነው የዜጎቻችውን እና የሀገራቸውን መብቶች በሚያስከብሩ ሃገራት ውስጥ ብቻ ነው።እኛን አይመለከትም።ቴዲ የኢትዮጵያ የክብር አምባሳደር ነው።በሄደበት ቦታ የሚያገኘው ክብር የእርሱ ክብር ብቻ ሳይሆን የሐገሩንም ክብር ነበር።የክዋታር መንግስት እና የሱዳን መንግስት በክብር (በፖሊስ ሞተር ሳይክል አጅበው የተቀበሉት ) ቴዲ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልሆነ ሳያውቁ ቀርተው አይደለም።ከጀርባው የያዘውን እና ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳስደመመ ስለሚያውቁ ነው።ይህ ጉዳይ ዓለም አቀፍ ጥቅምን እና ክብርን የማስከበር ጉዳይ ነው እንጂ የቴዲ ጉዳይ አይደለም። ደግሞስ መንግስት የሚባል ነገርዮ ያስፈለገው እንዲህ እንዲህ አይነት ሥራ እንዲሰራ ነው እንጂ አለበለዝያ ምን ይሰራል? የባለስልጣኖቻችን ዝምታ እንደተለመደው ሲያስገርመን ብቻ ሳይሆን ራዕይ እና ትልማቸውን ሁሉ ይተርክልናል።

2/ አንዳንድ የጎሳ ፖለቲካ የሚያራምዱ ቡድኖች ላይ የመረረ አቋም አለመውሰድ በራሱ ዋጋ እንዳለው መረዳት ይገባል።”አካፋን አካፋ” ማለት መልመድ አለብን።ኢትዮጵያውያን ነን።በኢትዮጵያ ጥቅሞች ላይ የሚሰነዘር ማናቸውንም ሲፈልግ የተንሸዋረረ የታሪክ ዕይታም ሲሻው የጎሳውን ትልቅነት እየሰበከ ይምጣ ልኩ ሊነገረው አደብ እንዲገዛ ማስተካከል ተገቢ ነው።የጎሳ ፖለቲካ የፋሽሽት እና የናዚዎች ወደ ስልጣን የመወጣጫ መሰላል ነች።ሞሶሎኔ የሮማን ሕዝብ ታላቅነት እየሰበከ ጦርነት አወጀ።ናዚዎች የጀርመንን ዘር ታላቅነት እየሰበኩ ዓለምን በደም ነከሩ።’ማንቆለጰላጠሱ’ ፋይዳ የለውም።የፋሽሽት እና የናዚዎች ርዕዮተ ዓለም በመሸፋፈን አይፈታም።ዓለም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሞክሮት አልተሳካለትም። ዛሬም ኢትዮጵያዊነትን በጎሳቸው ”ታላቅነት” በሚሉት የመለያያ ጉረኖ ሸፍነውና በተንሸዋረረ የታሪክ ዕይታ ተደብቀው የሚያምታቱ ሁሉ ማንነታቸውን አንጠርጥሮ ማጋለጥ ይገባል።

Advertisements