‹‹የተገኘውን ጫት አለመሸጥ ሞኝነት ነው የሚመስለኝ›› የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ


e832229497fb2577ef7a5704e6a736dd_Lየንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ የአሥር ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ ባቀረቡበት ወቅት፣ መንግሥት ከጫት ምርት ኤክስፖርት ያገኘውን የውጭ ምንዛሪ ይፋ አድርገዋል፡፡

ይሁን እንጂ አንድ የምክር ቤቱ አባል ወጣቱን እያበላሸ የሚገኘው የጫት ምርት ሊቀጥል ነው ወይ? ጫት በገበሬው ማሳ እንዳይስፋፋ ነው መደረግ ያለበት ወይስ እየተበረታታ እንደሔድ ነው? ያለው ወጣቱ የመንግሥት አቋም ምን እንደሆነ እንዲገልጽ ጠይቀዋል፡፡ ሚኒስትሩም ምላሻቸውን እንዲህ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ጫትን ለማበረታታት የምንሠራው ሥራ የለም ለግብርና ምርታችን የኤክስቴንሽን ሠራተኛ መድበን እናበረታታለን፡፡ የማዳበሪያና ሌሎችን ግብአቶችንም እናቀርባለን ምርጥ ዘርም እናቀርባለን፡፡ በጫት ላይ ግን የምንሠራው ምንም ድጋፍ የለም፡፡ ግን በራሱ ጉልበት እራሱ እየቀጠለ ነው፡፡

‹‹በራሱ ጉልበት ሲቀጥል እኛ እንደ ንግድ ሚኒስቴር እየሸጥን ተጠቃሚ መሆን አለብን፣ እየሸጥንም ነው፡፡ ስለዚህ መንግሥት አያበረታታም፣ አያዳክምም፡፡ ለማዳከምም ብሎ አትሽጡ ብሎ ነቅሎ (ከማሳ) ያቃጠለበትም አጋጣሚ የለም፡፡ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ለጊዜው ዝም ነው፡፡ አናበረታታም የጫት ተጠቃሚ የኅብረተሰብ ክፍል ስላለ ሸጠን መጠቀም ስላለብነ እየሸጥን ነው፡፡ ገቢውም ቀላል አይደለም፡፡ በዓመት እስከ 260 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይገኛል፤ ትልቅ አቅም ነው፤ እንሸጣለን፡፡

‹‹ዞሮ ዞሮ እኛ ጫት አታምርት ብንለውም አርሶ አደሩ ወደኋላ አይልም፡፡ ሐረርጌ በአብዛኛው ጫት ነው የሚያመርተው፡፡ ሔደን ጫቱን ንቀልና ሌላ ነገር እህል ወይም ቡና አድርገው ብንል እንኳ እሺ የሚል አይመስለንም፡፡ ማሳመን መቻል አለብን አርሶ አደሩን፡፡ እሱ ላይ ሳንሠራ አሁን የተገኘውን ጫት አለመሸጥ ሞኝነት ነው የሚመስለኝ ስለዚህ ሸጠን መጠቀነው፡፡››

ethiopianreporter

Advertisements