የብራዚልዓለም ዋንጫና ተቃውሞ


ከ ደረጀ አብተዎልድ
 
10325764_10202232412754284_7662465659685169351_nብራዚላውያን -መንግስታቸው ለዓለም ዋንጫ ዝግጅት ያወጣው ገንዘብ ከፍተኛ ነው በማለት ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ ሰነበቱ። በተለይ ሰሞኑን አዲስ በሚገነቡት ስታዲየሞች ዙሪያ የሚኖሩ ድሆች ለግንባታ ተብሎ ከቀያቸው መነሳታቸው ተቃውሞውን ከዳር እሰከ ዳር አቀጣጥሎታል። ሰልፈኞቹ በርካታ ንብረቶችን አቃጥለዋል፤አውድመዋል።ተቃውሞው ለሳምንታት ከመቶ በሚበልጡ ከተሞች የተቀጣጠለ ቢሆንም፤ እስካሁን የሞተው በሳዎ ፖሎ አንድ ሰው ነው። “ምን ሆኖ ሞተ?በማን ተገደለ?” አላችሁ?….ጥሩ ጥያቄ ነው። አንድ ሰው የሞተው ፤ በፖሊስ ሳይሆን በሰልፉ አጠገብ መኪናውን እያሽከረከረ ለማለፍ በሞከረ ሾፌር ተገጭቶ ነው።ፖሊሶች በድንጋይ ሲደበደቡና በትሩ ሲበሳባቸው የሚወስዱት እርምጃ በ አስልቃሽ ጭስ ሰልፈኞችን መበተን ነው።
የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀት ለአንድ ሀገር ከፍ ያለ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም( ልማት ቢሆንም) ፤መንግስት ደሀዎችን ከይዞታቸው ማፈናቀሉ ከዜጎች ደህንነት ይልቅ ለካዝናው መሙላት መጨነቁን ያሳያል በሚል ተቃውሞው አይሎ መንግስትን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። ተቃዋሚዎቹ በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅትም በስታዲየሞች አቅራቢያ ሆነው ተቃውሞአቸውን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ማሰማታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።
በመቶ ከተሞች ለሳምንታት የተቀጣጠለው ተቃውሞ እያደር እየተባባሰ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቢደርስም፤ከላይ እንደጠቀስኩት እስካሁን “ፀረ-ልማት” ተብሎ በፖሊስ አንድም ሰው አልተገደለም። ይልቁንም ሰልፈኞቹ ተቃውሞአቸውን ለበርካታ ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥሉ በማስታወቃቸው ውሃ፤ ግፋ ካለ አስለቃሽ ጪስ የሚረጩ በርካታ ፖሊሶች እየሰለጠኑ ይገኛሉ።
“ቤታችሁ በዶዘር እላያችሁ ላይ ቢፈርስም፤ ከቦታችሁ ብትፈናቀሉም ፤ለልማት እስከሆነ ድረስ መቃወም አትችሉም”፤እየተባሉ ሰዎች የሚገደሉባት(የሚታጨዱባት) ብቸኛ ሀገር ኢትዮጰያ ትመስለኛለች።
በልቶ ማደር ፈተና የሆነበት ብዙሀኑ ኢትዮጵያዊ “በልማት”ስም የተሸከመውን ቀንበር እና እየከፈለ ያለውን እዳ ሁላችንም እናውቀዋለን። ነገ ፍሬውን ለማያጣጥመው ልማት ህይወቱን እንዲገብር እየተደረገ ነው። “እኔ የምበላው አጥቼ በራብ እየተቀጣሁ ሳንቲም ማዋጣት ወይም ቦንድ መግዛት አልችልም” ብሎ መናገር የሚያስፈራበት ደረጃ ላይ መድረሱን እናውቃለን።አንድ ደሀ ይህን ቢል በ“ፀረ-ልማት” ፍረጃ ምን ሊደርስበርት እንደሚችል ያውቀዋልና። ስለሆነም ፦ “እህሉ የተዘራው ዛሬ ማታ፣ የሚደርሰው ለፍልሰታ፣ እስከዛው አንተ ሁነኝ ጌታ” በሚል የተስፋ መቁረጥ እንጉርጉሮ ከኖረበት ቀዬ እየተፈናቀለና አድርግ የተባለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
ወይ ሰው ገ’ሎ-ልማት!
“ሰው እየገደሉ ይማራል ወይ ነፍስ? “ ነበር የሚለው ዘፈናችን እንኩዋን
Advertisements