የአሜሪካ የሸፍጥ ዲፕሎማሲ “አስቂኝ የመድረክ ትወና” – ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም


የዩናይትድ ስቴትስ የመንግስት መምሪያ ጸሐፊ የሆኑት ጆን ኬሪ ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ፕሬዚዳንት ባሽር አላሳድን “አሸባሪ” ወንጀለኛ ናቸው ብለው ከፈረጁ በኋላ የአላሳድ የቀጣዩ ዓመት የምርጫ ዕቅድም “አስቂኝ የመድረክ ትወና” ነው ብለው ተችተው ነበር፡፡ ኬሪ በመቀጠልም እንዲህ በማለት ሀሳባቸውን አጠናክረውObama-San-Jose-AP-300x224 ነበር፣ “አሳድ ከአሸባሪ ኃይሎች ጋር ህብረትን ፈጥረዋል፣ አሸባሪዎችንም እያቀረቡ እና እየረዱ ነው፣ እናም በእራሳቸው ህዝብ ላይ አሸባሪነትን በመፈጸም ዕኩይ ተግባራት ላይ ተዘፍቀው ይገኛሉ፡፡“ እንዲሁም ኬሪ የሚከተለውን ነገር አጽንኦ በመስጠት ተናግረዋል፣ “የአሳድ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዕቅዶች ለታዕይታ የተዘጋጁ አስቂኝ የመድረክ ትወናዎች ናቸው፡፡ በዚህ መልኩ ለመተግበር የሚደረጉ ምርጫዎችም በህዝብ ላይ የሚካሄዱ ዘለፋዎች ናቸው፣ እንደዚህ ዓይነቶቹ ዕኩይ የምርጫ ዕቅዶች በሶሪያ እና በዓለም ህዝቦች ዴሞክራሲ ላይ የሚቃጡ ሸፍጦች ናቸው፣“ ብለው ነበር፡፡ American Diplocrisy Amharic Translation – PDF

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Advertisements