ሰበር ዜና: በአዲስ አበባ ታስቦ የነበረው የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሰልፍ ታገደ


 በአዲስ አበባ ታስቦ የነበረው የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሰልፍ ታገደ! እንዲሁም ታስቦ የነበረውና ግብረሰዶማዊነትን ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል ለማድረግ ለፓርላማ ቀርቦ redwa_vtim1-300x154የነበረው ረቂቅም ተሰረዘ

ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አሶስየትድ ፕሬስን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሰልፉ ታግዷል ብሏል። የመንግስት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሬድዋን ሁሴን የጠቀሰው ዘገባው “ጸረ ግብረሰዶማዊነት ስልፍ የተዘጋጀው በግለሰቦች እንጂ በመንግስት አይደለም፣ እናም ከዚህ በላይ ነገሩን ማቀጣጠል አንፈልግም” ማለታቸውን ጠቅሷል። አያይዞም “ታስቦ የነበረውና ግብረሰዶማዊነትን ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል ለማድረግ ለፓርላማ ቀርቦ የነበረው ረቂቅም ተሰርዟል፣ ግብረሰዶማዊነት እንደሚወራው የተስፋፋ አይደለም፣ አሁን ያለው ቅጣትም በቂ ነው፣ ከዚህ በላይ የሚጋነን ወንጀል አድርገን አናየውም” ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዛሬ ዘግቧል። በሌላ በኩል የጸረ ግብረሰዶም ሰልፉን በማስተባበር ላይ የሚገኘው ወጣት ደረጄ “ሰልፉን በማዘጋጀቴ ከግብረሰዶማውያን ቡድኖች ትልቅ ማስፈራራት እየደረሰብኝ ነው” ማለቱን ጠቅሷል።

የዋሽንግተን ፖስትን ሙሉ ዘገባ ይህን ተጭነው ያንብቡ==>http://goo.gl/fBQobp