የአንድ ቀን የፕሬዚዳንት ኦባማ ጉበኝት ቤልጂየምን 10 ሚሊየን ዩሮ አስወጥቷል


Obama  visit to Belgiumየአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቤልጂየም ያደረጉት የአንድ ቀን ጉብኝት መዲናዋ ብራሰልስን 10 ሚሊየን ዩሮ አስወጥቷል።

የአውሮፓ ህብረት እና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ መቀመጫ በሆነችው ብራሰልስ ፕሬዚዳንት ኦባማ ትናንት የአንድ ቀን ቆይታ ቢኖራቸውም የፀጥታ ጥበቃ ስራው ከተማዋን ብዙ አስወጥቷታል ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ቤልጂየም ብራሰልስ ሲጓዙ አብረዋቸው 900 የፀጥታና ሌሎች ሰራተኞችን፣ 40 ተሽከርካሪዎችንና ሶስት የትራንስፖርት አውሮፕላኖችን ይዘው ነው።

የከተማዋ ከንቲባ እንዳሉት፥ በተደጋጋሚ የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን የምታስተናግደው ብራሰልስ በጉባኤዎቹ ወቅት በቀን ለፀጥታ ጥበቃ አውጥታ የምታውቀው ግማሽ ሚሊዮን ዩሮ ብቻ ነው።

የአሁኑ የኦባማ ጉብኝት ያስወጣው ወጪ ግን በ20 እጥፍ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

ከተማዋ ለኦባማ የፀጥታ ጥበቃ 350 የፀጥታ ሀይሎች፣ ዘጠኝ ሄሊኮፕተሮችና 30 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን አሰማርታ ነበር።

ምንጭ፦ ዘጋርዲያን

Advertisements