በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው?


ማነው ሲምካርድ? ማነው ቀፎው?

sim-620x310

በአሁኑ ሰዓት ጦቢያን የሚመራት ማነው “Who is in Charge?” የሚለው ጥያቄ ያሳሰባቸው ቧልተኞች  የፈጠሩትን ቀልድ ላልሰማችሁ ላሰማችሁ፡፡ (ኮፒራይቱ የሰፊው ህዝብ እንደሆነ ይታወቅልኝ!)
አንዱ ኤፍኤም ሬዲዮ ይደውላል – ዘፈን ለመምረጥ።

ደዋይ – ዘፈን ለመምረጥ ነበረ፤ የእገሌን …
ኤፍ ኤም- ማን እንበል? ከየት ነው?
ደዋይ-    የገዢው መደብ አባል ነኝ—- ከደቡብ!
ኤፍ ኤም- (ደንገጥ ብሎ) ከደቡብ … እሺ ዘፈኑ ይቀጥላል …
(የኤፍኤሙ ጋዜጠኛ ከድብልቅልቅ ስሜት ሳይወጣ ሌላ ዘፈን መራጭ ይደውላል)

ኤፍ ኤም- ሄሎ … ማን እንበል? ከየት ነው?
ደዋይ –    ዘፈን ለመምረጥ ነበር
ኤፍኤም- ራስህን አስተዋውቀን?
ደዋይ –    የገዢው መደብ አባል ነኝ – ከትግራይ!
ኤፍኤም – እንዴትነው ነገሩ? አሁን ከደቡብ ደውሎ የገዢው መደብ አባል ነኝ ብሎኛል እኮ?
ደዋይ- ዝም ብሎ ነው ባክህ … እነሱ ቀፎ፤ እኛ ሲም ካርድ ነን! …”

(ምንጭ: አዲስ አድማስ “ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም እየመሩን መሆናቸውን ለምን ተጠራጠርን?” ከሚለው መጣጥፍ የተወሰደ)

Advertisements