ኦባማና ቢዮንሴ በፍቅር ጦፈዋል” እየተባለ ነው


Eollywood.com
ku-xlargeየትውልድ ቦታቸውና ዜግነታቸው ትልቅ ጥያቄ ውስጥ ሆኖ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አሁን ደግሞ ከድምጻዊት ቢዮንሴ ጋር በፍቅር ጦፈዋል የሚል ወሬ እየተወራባቸው ነው፡፡

ሰኞ ዕለት የፈረንሳዩ ፎቶ አንሺ ይህንን ዜና ተናገረ ከተባለ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ የበርካታ ጋዜጦችን ቀልብ የሳበ ዜና ሆኗል፡፡
ፎቶ አንሺው ጋዜጠኛው አለ ተብሎ የተዘገበው ዜና እንደሚያመለክተው ከሆነ የ52ዓመቱ ኦባማ ከ32ዓመቷ የጄዚ ባለቤት ቢዮንሴ ጋር በድብቅ ሲፋቀሩ ከርመዋል፤ ዜናውንም ዋሺንግተን ፖስት ዛሬ ማክሰኞ ይፋ ያደርገዋል የሚል ነበር፡፡ የዋሺንግተን ፖስት ግንኙነት ኃላፊ ጋዜጣው እንዲህ ዓይነት ዜና እንደማያትም “በእርግጠኛነት እናገራለሁ” ካሉ በኋላ ግን ሁኔታው መቀየር ጀምሯል፡፡

ቀጥሎም ዜናውን የሰበረው ፈረንሳዩ ፎቶ አንሺ “እኔ ይህንን ሁሉ አላልኩም” በማለት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ሆኖም አንዳንድ የአሜሪካ ጋዜጠኞች በጉዳዩ ላይ እየሠሩበት ነው በማለት ቃሉን አስተካክሏል፡፡ ሲቀጥልም “በባራክ ኦባማና በባለቤታቸው ሚሼል መካከል ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ሁኔታዎች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደማይገኙ፤ እኔም እስከማውቀው ድረስ ግንኙነታቸው እየቀዘቀዘ መምጣቱ ከማወቅ በላይ ሌላ የማውቀው ነገር የለም” በማለት ምላሹን ሰጥቷል፡፡

ስለፍቅራቸው ዓለም የዘፈነላቸው ባራክና ሚሼል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚታዩባቸው ቦታዎች በአብዛኛው እንደቀድሞ ከመቀራረብ ይልቅ የቀዘቀዘ ግንኙነት እንዳላቸው የሚያመላክቱ ሁኔታዎች በተደጋሚ ሲስተዋሉ ሰንብተዋል፡፡ ሁኔታውን በተለያየ መንገድ የሚተረጉሙ ተንታኞች ቀድሞውኑም ነበረ የተባለው “ፍቅር” የታይታና ለካሜራ ፍጆታ እንዲሆን የታሰበበት ድራማ ነው ቢሉም ሌሎች ግን በባልና ሚስቱ መካከል ያለው ግንኙነት ከቀድሞው ምንም የተቀየረ እንዳልሆን ይናገራሉ፡፡

(የዜናው አብዛኛው ክፍል የተጠናቀረው ከ Daily Mail እና Huffington Post ነው)