ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ሆኑ


GizachewShiferawየአንድነት ፓርቲ ድርጅቱን ለቀጣይ ዓመታት የሚመራውን ፕሬዚዳንት ለመምረጥ በጠራው ጉባኤ ላይ በተደረገ ምርጫ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን ለዘ-ሐበሻ ከአዲስ አበባ የመጣው መረጃ አመለከተ።

ከፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ ስልጣኑን የተረከቡት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ከርሳቸው ጋር ለውድድር ቀርበው የነበሩት በፓርላማው ውስጥ ያሉት ብቸኛው ተቃዋሚ አቶ ግርማ ሰይፉ እና አቶ ተክሌ በቀለ የነበሩ ሲሆን ኢንጂነር ግዛቸው ከተመዘገበው 290 መራጭ ውስጥ 227ቱን በማግኘት አሸንፈዋል።

በዚህ ምርጫ ላይ በተፎካካሪነት ቀርበው የነበሩት አቶ ተክሌ በቀለ ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ኢንጂነር ግዛቸው ከዚህ ቀደም አንድነት ፓርቲን ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በምትመራበት ወቅት ምክትል ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

Advertisements