በሄትሮ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኢትዮጵያ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን የሙከራ በረራ እያደረገ ነው


945190_707980329224731_1702917653_nአዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል በለንደኑ የሄትሮ አውሮፕላን ማረፊያ ጉዳት ደርሶበት የነበረው ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላን አገልግሎት እንዲቀጥል ለማድረግ የሙከራ በረራዎችን እያደረገ ነው።

አየር መንገዱ በቀጣይ አውሮፕላኑ የአለምአቀፉን የበረራ ፈቃድ አግኝቶ ዳግም ወደ በረራ እንዲመለስ ለማድረግም እየሰራ መሆኑ ነው የገለፀው ።
አውሮፕላኑ በርከት ያሉ የሙከራ በረራዎችን ያደረገ ሲሆን ፥ በትናንትናው እለትም እስከ 39 ሺህ ጫማ በመብረር የበረራ ብቃቱን ለክቷል።
አለም አቀፍ የበረራ ፍቃድን ዳግም ለማግኘት ይህን መሰል የሙከራ በረራዎች የተለመዱ መሆናቸውን የጠቆመው ዘገባው ፥ የኢትዮጵያ አውሮፕላንም አለም አቀፍ ፈቃድ ሊያሰጠው የሚችለውን በረራ በማድረግ በቃቱን በመፈተሽ ላይ መሆኑን ገልጿል።

Advertisements