ማሊ በሚገኝ ራዲሰን ብሉ ሆቴል 170 ሰዎች በታጣቂዎች እንደታገቱ ናቸው

mali_attack በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ በሚገኝ አለም አቀፍ ሆቴል ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸው ተሰማ።

ጥቃቱ የተፈጸመው በአሜሪካውያን በሚተዳደረው የራዲሰን ብሉ አለም አቀፍ ሆቴል ነው።

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት በሆቴሉ ህንጻ ሰባተኛ ወለል ላይ ሲሆን፥ 30 የሆቴሉን ሰራተኞች ጨምሮ 170 ሰዎችን አግተዋል።

mali_attack.jpg

እስካሁን ሶስት ታጋቾች ሲገደሉ፥ 80 ያህሉ ደግሞ ከእገታው ድራማ ነጻ መሆናቸው እየተገለጸ ነው።

3 የቱርክ እና 12 የፈረንሳይ አየር መንገድ ሰራተኞች እና ጊኒያዊው ሙዚቀኛ ሴኩባ ባምቢኖ ከተለቀቁት መካከል ይገኙበታል።

የማሊ ልዩ ሃይል ወደ ሆቴሉ በመግባት ቀሪ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ባደረጉት ጥረት ሁለት አባሎቻቸው መጎዳታቸውን ከቢቢሲ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የሃገሪቱ ደህንነት ሚኒስትር ሳሊፍ ትራኦሬ ሆቴሉ አቅራቢያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ጥቃት አድራሾቹ እንደማያመልጡ ተናግረዋል።

ፈረንሳይ በበኩሏ 50 የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል አባላትን ከፓሪስ ወደ ባማኮ ልካለች።

ታጣቂዎቹ በዲፕሎማት መስተንግዶ ወደ ሆቴሉ ለመግባት መሞከራቸውን እና ዘግየት ብለው የተኩስ ልውውጥ መክፈታቸውን አንድ የሆቴሉ አትክልተኛ ተናግሯል።

በታጣቂዎቹ ከታገቱት መካከል፥ ይህንድ፣ የቻይና፣ ፈረንሳይና የቱርክ ዜጎች ይገኙበታል።

እስካሁን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ ቡድን ባይኖርም ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚታመኑ ጽንፈኛ ታጣቂዎች ሳይሆኑ እንደማይቀር መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሃገሪቱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የሚፈጽሙት አክራሪ እስላማዊ ታጣቂዎች ሰሜናዊ የሃገሪቱን ክፍል በስፋት ተቆጣጥረውታል።

ሆቴሉ በሃገሪቱ በሚሰሩ የውጭ ዜጎች የሚዘወተርና ተመራጭ መሆኑን ዘገባዎች ያሳያሉ።

Advertisements